እኛ የምንፈልገው ተግባር ነው:- በኪንግ ካውንቲ ወረርሽኝ ምላሽ ላይ የተሰጠው ሐሳብ

በአቶ በረከት ኪሮስ እና ካርላ ሂሜነዝ-ማግዴሌኖ

ማስታወሻ፤ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የቆዳ ቀለም ባለባቸው ማህበረሰቦች ላይ የሚታየውን ኢ-ፍትሃዊነት አጉልቷል። የማህበረሰብ ጤና ማዕከል ቀደም ብሎ በ2020 ይህ ሊከሰት እንደሚችል እውቅና ሰጥተዋል ፤ ምክንያቱም በሽታዎች ከመዋቅራዊ ዘረኝነት ጋር ሲገናኙ ሁል ጊዜ የሚከሰት ነው። ከዛ እውቅና በመነሳት - በተጨማሪም የሌሎች አስተያየት አስፈለጊ በመሆኑ እና በሁሉም ዘርፎች ላይ ያመጣውን ተፅዕኖ ለመፍታት የወረርሽኝ የማህበረሰብ አማካሪ ቡድን ተመሰረተ:: የቡድኑ መዋቅር የቀድሞ የኪንግ ካውንቲን ልምድ ያንፀባርቃል፡፡ ይኸዉም ከማህበረሰብ ፣ ከንግድ ስራ ፣ ከትምህርት እና ከድርጅት ዘርፎች የተውጣጡ መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ በተጨማሪ በተቋማት የተገለሉ ማህበረሰቦችን በተለይ ስደተኞች እና ጥቁሮች፤ ነባር ተወላጆች እና የቆዳ ቀለም ያላቸውን ማህበረሰቦችን ያካተተ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ዘረኝነት የማህበረሰብ ጤና መቃወስ እንደሆነ በወጣው መግለጫ መሰረት፤ እነዚህ የወረርሽኝ እና ዘረኝነት ማህበረሰብ አማካሪ ቡድንኖች (ድህረገፁ በእንግሊዝኛ ነው) ለኮቪድ-19 የሚሰጠውን ምላሽ ለሁሉም ዘር እኩል ተደራሽ እንዲሆን እና የዘረኝነት መንስኤዎችን ለመፍታት ኃላፊነቱን ይጋራሉ፡፡

ለአቶ በረከት ኪሮስ ያለፈዉ የወረርሽኝ አመት ባያስገርምም አድካሚ ነበር፡፡

በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ኪንግ ካውንቲ ከሌሎች ያአሜሪካን ካውንቲዎች የተለየ አይደለም፡፡ የኮቪድ-19 ክትባቶች በ2021 ለመጀመሪያ ጊዜ መሰጠት ሲጀመር፣ ምንም እንኳን በዘር የተለያዩ ማህበረሰቦች በስፋት በሚኖሩበት በደቡብ ኪንግ ካውንቲ ውስጥ የኮቪድ-19 ክስተቶች በጣም ከባድ የነበረ ቢሆንም ፤ ክትባት የወሰዱት ህዝቦች ቁጥር ነጮች እና ሃብታሞች በብዛት በሚኖሩባቸው እንደ ቫሾን እና ሰሜን ሲያትል ባሉ ስፍራዎች ከፍ ያለ ነበር፡፡

ኪሮስ የኮቪድ-19 በሽታ በኪንግ ካውንቲ ሲታይ እነዚህን ተደጋጋሚ (ሆኖም ሊታረሙ የሚችሉ) ዘረኛ እና የመደብ ኢፍታዊነቶች እንደሚከሰቱ ጠብቆ ነበር፡፡ ሆኖም ኪሮስ እንደ ማህበረሰብ በአጠቃላይ ማህበረሰባችን ፍታዊ ተጠቃሚነቱን መልሶ እንዲያገኝ በእውነት ልንረዳው እንደምንችል ያምናል፡፡

ኪሮስ ልክ የመጀመሪያው የኮቪድ-19 በሽታ ከታየ በኃላ ወዲያውኑ ከኪንግ ካውንቲን የወረርሽኝ እና ዘረኝነት ማህበረሰብ አማካሪ ቡድን (ድህረገፁ በእንግሊዝኛ ነው) (ፒኤአርሲኤጂ/PARCAG) ጋር ተቀላቅሏል፡፡  ፒኤአርሲኤጂ (PARCAG) ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ዘረኝነት ምላሽ ለመስጠት ከመንግስት እና ከማህበረሰቡ የተውጣጣ በጋራ የተመሰረተ ቡድን ነው፡፡

በረከት ኪሮስ ከሲያትል ከተማ ጋር ስብሰባ እያደረጉ።

ኪሮስ የስደተኞች፣ የረፊውጅ፣ እና የቆዳ ቀለም ያላቸው ማህበረሰቦች ጥምረት (CIRCC) (ድህረገፁ በእንግሊዝኛ ነው) ሊቀመንበር/መስራች በነበረበት እና የኮቪድ-19 የማህበረሰብ ምላሽ ጥምረት (The Alliance) በሆነበት ጊዜ ያገኘውን የብዙ አመታት የማህበረሰብ ግንባታን ልምድ እና እውቀት ወደ ፒኤአርሲኤጂ (PARCAG) አምጥቷል፡፡ ጥምረቱ ከ17 በላይ የሚሆኑ የብዙ ዘሮች፣ ባህል እና የቋንቋ ድርጅቶችን ያካትታል፡፡

እንደ ፒኤአርሲኤጂ (PARCAG) የኮሚቴ አባልነቱ መሰረት የፀረ-ዘረኝነት መነፅርን ተጠቅሞ ለወረርሽኙ ምላሽ ለመስጠት እንዴት ማህበረሰቡን በአጠቃላይ እንደሚረዳ ለማወቅ ከኪሮስ ጋር ተገናኘሁ። 


ይህ ቃለ መጠይቅ ግልፅ እንዲሆንና እንዳይረዝም ሲባል ታርሞ ቀርቧል ፡፡

አቶ ኪሮስ እስኪ ስለ እራሶት ትንሽ ይንገሩን፡፡ እንዴት ነው የህይወት ልምምዶት እርሶን ወደ (PARCAG) ፒኤአርሲኤጂ እንዲቀላቀሉ የመራዎት?

በረከት ኪሮስ፡ የተወለድኩት በኢትዬጰያ ውስጥ ሲሆን በ1985 ወደ ሚልዋውኪ ከመዛወሬ በፊት አብዛኛውን ቀደም ብሎ ባሉት አመታት በአውሮፓ በመዘዋወር አሳልፊያለሁ፡፡

በሚልዋውኪ የነበረው የዘረኝነት ውጥረት አስደንጋጭ ነበር፡፡  አንድ የካቶሊክ ስፖንሰሬ የነበረ እስያዊ አሜሪካዊ ከአየር መንገድ ተቀብሎኝ ወደ ተመደብኩበት የጥቁሮች ሰፈር እንደወሰደኝ አስታውሳለሁ። እንደደረስን “እዚህ አትኖርም!” አለኝ፡፡ በጣም ስለተጨነቀም ለ 6 ወራት በራሱ ቤት አኖረኝ።

አሜሪካ አስተማማኝ ስላልነበረች  እና ወደ መጣሁበት ለመመለስ አስቤ ነበር፡፡ የዘር መከፋፈሉ የማይታመን ነበር፡፡ ሃገሩን ለቅቄ እንደመሄድ፤ በ1991 ለትምህርት ወደ ሲያትል ተዛወርኩኝ፡፡ የዛው አመት ላይ የትግራይ ማህበረሰብ ማዕከል ባገኝ ብዬ አለምኩኝ፡፡ ስለዚህም፣ በደረስኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ አንድ አቋቋምን፣ እርሱም በሲያትል ሁለተኛው የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ማዕከል ሆነ፡፡ በጥቂት ደረጃ ለህብረተሰቡ አገልግሎቶችን እና ንብረቶቻቸውን ማስቀመጫ ስፍራ በመስጠት ጀመርን፡፡

እኔ በሌሎች ጥቂት ፕሮጀክቶች እሳተፍ ስለነበር የአፍሪካ ሚዲያ ማህበር በዋሽንግተን መሰረትኩኝ፡፡ የራሳችን ሚዲያ ከሌለን ከማህበረሰባችን ጋር ለመገናኘት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ በመጨረሻም ለሲያትል ከተማ ለ12 ዓመታት ሰራሁ፡፡ እዚያ ነበር ስለ “ማህበራዊ ፍትህ” ፅንሰ-ሐሳብ የተማርኩት፡፡ ያ ነበር ተመልሼ ወደ ትምህር ት ቤት በመግባት ማስትሬት ድግሪዬን (ኤምቢኤ) እንድይዝና ለማህበረሰቤ ድምፅ በመሆን እውቀቴን መጠቀም እና ሌሎችም ከኔ ጋር እንዲቀላቀሉ ለማበረታታት ያነሳሳኝ፡፡

የህይወት ልምዶ በፒኤአርኤጂ (PARCAG) ባሎት ሚና ለለውጥ ጥብቅና የቆሙበትን መንገድ  እንዴት ተፅኖ አድርጎበታል?

በምዕራብና በምስራቅ የህይወት ዘይቤ ውስጥ መኖሬ ስለ ሰው ልጅ የተለየ አመለካከት እንዲኖረኝ አድርጎኛል፡፡ ተሳትፎን በተመለከተ ብዙ እንድሰራ እና አንድነትን ለመፍጠር የጋራ የሆኑንን ነገሮች ለመለየት እንድጥር ረድቶኛል፡፡ ሰዎች የራሳቸው የሆነ ድምፅ ሊኖራቸውና ሊሰሙም ይገባል፡፡

በምዕራቡ አለም ላይ ለውጥን ለማምጣት ወደ ጦርነት መሄድ እንዳለብህ ይሰማሃል፡፡

በፒኤአርኤጂ (PARCAG)፣ ኪንግ ካውንቲ ማንነታችንን ለመግለፅ ስፍራ ይሰጠናል፡፡ አብዛኛው ትልልቅ ድርጅቶች እና ኮርፖሬሽኖች እራሳቸውን መግለፅ ይችላሉ፡፡ ባለሙያዎችን ይልካሉ፣ ጥናት ያደርጋሉ፣ ጥያቄ ይጠይቃሉ እናም  አንተን ወክለው ባለሙያዎች ይሆናሉ፡፡ ይህ የማይረዱ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

በፒኤአርሲኤጂ (PARCAG) ለማህበረሰቤ እንደ መልክተኛ ሆኜ እንድናገር ረድቶኛል፡፡ ፈታሾች እና ጠያቂዎች የሁለትዮሽ ውይይት መንገድ ፈሯርዋል፡፡ ፓቲ ሄይስ /የቀድሞ የማህበረሰብ ጤና ዳይሬክተር/ ወደ ስብሰባዎች በመሄድ የኮቪድ-19 በሽታን ጠቋሚዎችን ታካፍላለች እና እየተጋፈጥን ያለውን ፈተናዎችን እና ሁኔታዎችን ታብራራለች፡፡

ይህ ጥሩ ጅማሬ ነው ምክንያቱም ያለ ፒኤአርሲኤጂ (PARCAG) ከነዚህ ትላልቅ ድርጅቶች እኩል መሰማት በጣም ከባድ ነው፡፡ ስለ ማህበረሰባችን ተግዳሮቶች እንነጋገራለን፡፡ ይኸውም በአለው ስርዓቶች እና በሰዎች መካከል መግባባትን ለመፍጠር የመጀመሪያው እውነተኛ እርምጃ ነው፡፡

ለማህበረሰብዎ መልእክተኛ እንዲሆኑ ፒኤአርሲኤጂ (PARCAG) እንዴት ያንን ሁኔታ እንደፈጠረ ምሳሌ ይጥቀሱልን?

መጀመሪያ ላይ ካውንቲው፣ የሲያትል ከተማ እና የዋሽንግተን ዩንቨርስቲ በኮቪድ-19 ዙሪያ የሰበስቡበት መረጃዎች በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነበር፡፡

ለምሳሌ እኔ የስካን (SCAN) ጥናት (ድህረገፁ በእንግሊዝኛ ነው) አካል ለመሆን ስመዘገብ, የ17 ገፅ ጥናት ተቀብያለሁ፡፡ ጥናቱን በስተጀርባ የሰሩ እውነተኛ ሰዎች አልነበሩም፣ ስለዚህም ማንም ስለ ጥናቱ ሊረዳ የሚችል የለም፡፡ በመጨረሻም የጥናቱ ውጤት ያልተሟላ ነበረ፡፡ የቀድሞ የድግሪ ተማሪ እንደመሆኔ መጠን ጥናቱን ለመረዳት ተግዳሮቶች ነበሩብኝ፡፡ ሌሎችን አስቡ! ይህንንን ጥናት የቆዳ ቀለም ያላቸውን ማህበረሰብዎች ለመርዳት እምትሞክር ከሆነ፣ ልምዱን ቀለል ማድረግ አለብህ፡፡ የችግሩ አካል የሆነው ብዙዎቹ የጥናቱ መሪዎች ነጮች መሆናቸው ነው፡፡

እኔ በፒኤአርሲኤጂ (PARCAG) አባል ስለሆንኩኝ ይህንን የመረጃ አሰባሰብ አቀራረብን ለዶ/ር ጄፍ ዱቺን መቃወሜን ማሳወቅ ችያለሁ፡፡ እናም እሱ የተሻለ ስራ ልንሰራ እንደምንችል አምኖ ተቃውሞዬን ተቀብሏል፡፡ ዶ/ር ዱቺን አድርጎት የነበረው ጉዳዩን እውቅና በመስጠት ዩኒቨርስቲው ክትትል እንዲያደርግ እና የጥናቱ ተወካዬች ለውጥ እንደሚያስፈልግ ትኩረት እንዲሰጡ ነበር፡፡ ያደግሞ ያለ ፒኤአርሲኤጂ (PARCAG)  ሊሆን አይችልም ነበር፡፡

ለኮቪድ-19 ምላሽ በመስጠት ፒኤአርሲኤጂ (PARCAG) የመንግስትን ምላሽ እንዴት መቀየር ችሏል ብለው ያስባሉ?

ለውጥ ዝግመታዊ ነው፡፡ እኛ ደግሞ ትዕግስት የለንም፡፡ እኔ ያስተዋልኩት ነገር ለውጥ ቀስ እያለ ይመጣል፣ ስለዚህም እንታገስ እና አሁንም አሁንም ያለመታከት መጣር አለብን፡፡

በፒኤአርሲኤጂ (PARCAG) ውስጥ እኛ እንዴት ጥሩ ግንኙነት ማድረግ እንደምንችል ግንዛቤ ፈጥረናል፡፡ እኛ የማህበረሰባችንን መልዕክቶች ውሳኔዎች ላይ ተፅዕኖ ሊያደርጉ ወደሚችሉ ሰዎች እያስተላለፍን ነው፣ እናም ይህ በፒኤአርሲኤጂ (PARCAG) ከሚደረጉት ታላላቅ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

የተደራራቡ ችግሮች ውስጥ እንዴት ማለፍ እንዳለብን መማር ይኖርብናል፡፡ በጀት በጣም አስፈላጊ ነው፣ በበጀቶቻችን ውስጥ ለውጥን ካላካተትን ምንም አይነት ለውጥ ማግኘት አንችልም፡፡

ወረርሽኙ እንደጀመረ ለኪንግ ካውንቲ የቆዳ ቀለም ያላቸውን ማህበረሰብዎች ፣ የሰዎቹን የትውልድ ሀገር አካቶ (ሌሎች ምክንያቶች ጨምሮ) ለመደገፍ የተሰራውን ጥሩ መረጃ እንዲሰጡኝ በኢሜል ጠይቄ ነበር፡፡ ሆኖም ይህ በማህበረሰቡ በኮቪድ-19 በሽታ በመሰቃየት ላይ ያሉትን በማያገል መንገድ መሆን አለበት፡፡ የእኛን መረጃዎቻችን እንዴት እነደምንተነትን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡

ብዙ የማህበረሰቡ ድርጅቶች በፒኤአርሲኤጂ (PARCAG) ውስጥ ስለተወከሉ፣ ቡድናችን ትልቅ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል፡፡ የተመረጡት ባለስልጣናት ያዳምጡናል። ድርጅቶቻችን ከፒኤአርሲኤጂ (PARCAG) ጋር ከተቀላቀለ በኃላ ከሲያትል ፋውንዴሽን እና ከኪንግ ካውንቲ ብዙ ገንዘብ ማግኘት ጀመረናል። እኛ የቆዳ ቀለም ያላቸውን ማህበረሰብዎች ገንዘብ እና የሀብት ማምጫመንገዶች እና ድምፅ ሆነናል፡፡ እነዚህ ለትላልቅ ድርጅቶች ይሰጡ የነበሩ ገንዘቦች አሁን ማህበረሰባችን እየተቀበላቸው ነው፡፡

እስኪ ይህን በመንግስት የኮቪድ-19 ምላሽ እና በማህበረሰቡ ፍላጎት መካከል ስላለ መለያየት የበለጠ ይንገሩን?

አንዳንዶቻችን ስለ ማህበረሰብ ጥብቅና በፍቃደኝነት ላይ ያለመታከት እንሰራለን፡፡ ይህን የምናደርገው በራሳችን እምነት ፅናት ነው፡፡ ሆኖም የምንሰራው ስራ የህዝብ አገልግሎት ነው እና መንግስትን እንድንረዳ ከተፈለገ ደሞዝ ሊከፈለን ይገባል፡፡

እኛ ለማህበረሰባችን ስለምንጨነቅ የቆዳ ቀለም ያላቸውን ማህበረሰብዎች ያለ ክፍያ ይሰራሉ የሚል የተሳሳተ ግምት አለ፡፡ ነገር ግን መንግስት በዚህ ስራ ላይ ለሚሳተፉ ሰዎች በጀት ሊኖረው ይገባል፡፡ ቤተሰቦቻችንንም መደገፍ አለብን፡፡ እመነኝ፣ በጣም አድካሚ ስራ ነው፡፡ 

በመጨረሻ፣ ለማህበረሰቡ የምታደርገው ማንኛውም ነገር፣ ለወደፊት የሃገርን እጣ ፈንታ እያስተካከልክ እና ለውጥ ለመፍጠር ለምትፈልገው ህዝብ እየሰራህ ነው፡፡

ከዚህ ወረርሽኝ በኃላ በቀጣዩ ምን ሊፈጠር ይችላል ብለው ያስባሉ?

ለመጪው አመት ቀጣዩ ምን እንደሆነ መንግስት ያውቃል እሱም ማህበረሰባዊ ጥብቅና ነው፡፡ ለውጥ ላለማምጣት ምንም ሰበብ አይኖርም፡፡

በርግጥ የመቶ አመታት ጭቆናን በሳምንት ወይም በአመት ውስጥ ይፈታል ብዬ አላምንም፡፡ ሆኖም እድገትና የተሻሻለ ግንኙነት ልናይ እንችላለን፡፡ እና በዚህ እድገት፣ ማለቴ መለኪያዎች  ያደረግናቸውን ለውጦች ምን እንደሆኑ መለካት አለብን። ተጠያቂነትን የሚያሳይ፡፡የምናሳየቸውን ለውጦች መለኪያ ሊኖረን ይገባል፡፡

እስካሁን ማህበረሰቡ ምላሾችን መምራት እንዳለበት እና የፀረ-ዘረኝነትን እርምጃ መምራት እንዳለበት አውርተናል፡፡እነዚህን እንዴት ግብ ማድረስ እንችላለን ብለው ያስባሉ?

የጋራ በሆነ ድምፅ፡፡ ለዚህም ነው ለፒኤአርሲኤጂ (PARCAG) መስራት የምወደው፡፡

ለሀብት ስንል ለብዙ አመታት ተከፋፍለን ስንዋጋ ኖረናል፡፡ አሁን እንኳን አብሮ መስረት ከባድ ሊሆንብን ይችላል፣ እናም አንዳንድ ሰዎች እንደእኛ በጋራ ለመስራት ትልቅ መሆን አይፈልጉም፡፡ ሆኖም ድምፃቸው ያልተሰሙ ብዙ ማህበረሰቦች አሉ፣ ስለዚህ አብረን መስራት ይኖርብናል፡፡

አንተ ካለህ ልምድ ማህበረሰብህ ሊያውቅ ይገባል የምትለው ምንድን ነው? ካውንቲው እንዲረዳ የምትፈልገው ምንድን ነው?

ይህ በሂደት ላይ ያለ ስራ ነው፡፡ የጀመርናቸውን ስራዎች ሁሉ ልንከታተላቸው ይገባል፡፡ ይህ ስራ የአንድ ወቅት ጥብቅና ሊሆን አይገባም፣ ሁል ጊዜም መቀጠል አለብን፡፡ ገና መጀመራችን ነው፡፡

ለማህበረሰቤ፣ ሌሎችን መምከር ቁልፍ ስራ እንደሆነ እንዲያውቁ እፈልጋለሁ፡፡ ዘረኝነትን ከእያንዳንዱ ማህበራዊ ተቋም አንድ በአንድ ማፈራረስ እንዳለባቸው ይወቁ፡፡ ቀጣይነት ያለው ነው፣ ቀጣይነት የሌለው ማንኛውም ስራ አይሳካም፡፡ ለምናደርጋቸው አንዳንድ ስራዎች በህይወት ዘመናት ምላሽ ልናገኝላቸው እንችላለን፣ ለሌሎቹ ደግሞ ወደፊት የሚፈቱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

[ፎቶው] በረከት ኪሮስ ቀይ ሸሚዝ እና ኮፍያ አድርገው በፎቶው ላይ የማይታዩት የሲያትል ከተማ ከንቲባን ሲያነጋግሩ ነው።