1 ሚሊዮን ክትባቶች እና ቆጠራ: ከዚያ እንድንደርስ ለረዱን የማህበረሰብ አጋሮች ምስጋና ይድረሳቸው::

መጀመሪያ የታተመዉ አፕሪል 7 2021 ነው::

ኪንግ ካዉንቲ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡ አንድ ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶች ተሰጥተዋል።

ከአንድ ዓመት በፊት ያ የይቻል ይመስል ነበር። ግን ክትባቶች ርኮርድ በሰበረ ፍጥነት ነዉ የተሰሩት – አንድ ብቻ ሳይሆን፣ ሁለት ብቻ ሳይሆን ሶስት አዳዲስ ክትባቶች።  “ታላቅ እምርታ ነዉ ምክንያቱም በርካታ ህይወት ድኗል ማለት ነዉ” ብሏል አላን ላይ የቻይና ማህበረሰብ የማህበረሰብ አሳሽ እና አስተርጓሚ።  

በርካታ የማህበረሰብ እና እምነት ላይ የተመሰረቱ ድርጅቶች እንዚያን ክትባቶች በማድረስ ወሳኝ ሚና ተጫዉተዋል::

ይህ እምርታ ላይ መድረስ ምን ማለት እንደሆነ ሃሳብ እንዲሰጡ ከብዙ የማህበረሰብ አጋሮች ጋር ተነጋግረናል።

በጎ ፈቃደኞች ከክትባት ክልኒክ በኋላ ማርች 13 ሾርላይን ዉስጥ ተሰብስበዉ። (PHSKC/Erin Murphy)

መጀመሪያ ሚዛናዊነት

የማህበረሰብ ድርጅቶቻችን በኢንተርኔት ተደራሽነት፣ ቋንቋ ተደራሽነት፣ እና በህክምና ሥርዓት ዉስጥ ባለ የድሮ ዘረኝነት ገጠመኝ ጋር በተገናኙ እንቅፋቶች ቀጠሮ ለመያዝ የከበዳቸዉን ሰዎች ከክትባት ጋር ለማገናኘት ሰርቷል።   

አብዛኞቹ ቡድኖች የማህበረሰብ የክትባት መስጫ ኩነቶችን አደረጅተዋል። ሰዎችን ለከትባቶች በመመዝገብ ረድተዋል፤ ትራንስፖርት ለሌላቸዉ አዘጋጅተዋልም።

ባለማቋረጥ ከኮቪድ-19 ከባዱ ጫና  ያጋጠማቸዉ ቡድኖች፡ ስደተኞች፣ አፍሪካዊ አሜሪካዊ፣ ጥቁር ማህበረሰቦች፣ ላቲኒክስ ማህበረሰቦች፣ ነባር ተወላጆች እና ነባር አሜሪካዉያን፣ የፓሲፊክ ደሴት ነዋሪዎች፣ እና ሌሎች ነጭ ያልሆኑ ሰዎች ጋ በመድረስ  ለሚዛናዊነት ቅድሚያ ሰጥቷል።

“እንደ ሰደተኛ እና ነጭ እንዳልሆነ ሰዉ፣ ማህበረሰባችን በዚህ ወረርሽኝ በጣም ተጎድቷል”  ለማህበረሰብ ጤና የማህበረሰብ ትርጉም ክለሳ ቡድን አካል የሆነዉ መሐመድ ኻሊፍ እንደገለጸው:  “በርካታ ወሳኝ ሠራተኞች ያሉበት ባለ ብዙ ትዉልድ ቤተሰብ ዉስጥ ነዉ የምንኖረዉ። አብዛኞቻችን ማህበራዊ ርቀት ማድረግ እና ከቤት ሆኖ መሥራት አንችልም። ክትባት አስፈላጊ ነዉ ምክንያቱም የመሞት እና ኮቪድን የመቋቋም ልዩነት በመሆኑ።”

“በጣም ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦቻችንን ቅድሚያ በመስጠት በጽኑ እናምናለን” ብሏል የኪንግ ካዉንቲ ላቲንክስ ማህበረሰብ የሚደግፈዉ Villa Comunitaria አና ሶሌሮ።

የፊት ለፊት ሠራተኞችን እና ምግቦቻችንን የሚያቀርቡትን መደገፍ

ወረርሽኙ ከጀመረ ጀምሮ የተባበሩት የምግብ እና ንግድ ሠራተኞች ማህበር 21 አብዛኞቹ የወረርሽኙ ግንባር ላይ የሚሰሩ አባሎቻቸዉን ለመከላከል ቀን እና ሌሊት እየሰሩ ነዉ።

“ሌላዉ ዓለም ወደ ቤት እንዲሄዱ እና ማሻቀቡ እንዲያቆም እንዲረዱ ሲነገረቸዉ የኛ ባልደረቦች ግን ለሁላችን ሲሉ ስራቸውን ቀጠሉ” አሉ ሳማንታ ግራድ  የማህበሩ ፖለቲካ እና ህግ ዳሬክተር።

በርካታ ሠራተኞች ለቁርጠኝነታቸው ዋጋ ከፍለዋል ብሏል አና ሚናርድ የ UFCW21 መገናኛ ዳሬክተር። አንዳንዶች በኮቪድ-19  ታመው  ለቤተሰብ አባሎቻቻዉ አሰረጭቷዉ ሞተዋል።

“የአዕምሮ ጫናዉ ትልቅ ነዉ” አለ ግራድ። “እያንዳንዱ ደህንነት እና ጥበቃ እንደሰማዉ ለማረጋገጥ ቆርጠናል።”

ጃንዋሪ እና ፌብሯ 2021, UFCW21 ሁለት በዕድሜ ለገፉ ግሮሠሪ ሠራተኞች እና ባለብዙ ትዉልድ ቤቶች ዉስጥ ለሚኖሩ ሰዎች የክትባት ክሊኒክ በማደረጀት የሲያትል ከተማን ረድቷል። እነዚህ ኩነቶች በጆርጅታዎን ማህበር አዳራሽ ነዉ የተካሄዱት።

በዋሽንግተን ስቴት ባሉ ሜዳዎች እና የፍራፍሬ ማሳዎች በወረርሽኙ ጠቅላላ ወቅት የእርሻ ሠራተኞች የ UFCW21 አባላት የሚያዘጋጁት እና የሚያቀርቡት ሰብሎችን መትከል እና መሰብሰብ ቀጥሏል። 

እነሱን መከላከል ባልተካለለዉ የሬድመንድ ክፍል ያሉ የእርሻ ሠራተኞች ክትባቶችን እንዲያገኙ የሚረዳ ድርጅት የሆነዉ  የSound Sustainable Farms (በእንግልዝኛ ብቻ) ቅድሚያ የሚሰጠዉ ነዉ።

“የእርሻ/ግብርና ሠራተኞች የወረርሽኙ ዋና ጀግኖች ናቸዉ” አሉ ካረን ዳዉሰን ለቡድኑ የህዝብ ጉዳይ ዳሬክተር።

የሷ ድርጅት ነጭ ያልሆኑ ሰዎች እና እንግልዝኛ እንደ አንደኛ ቋንቋ ለማይናገሩ ክትባት ቅድሚያ እንዲያገኙ ለመረጋገጥ ትኩረት ያደርጋል።

“ሰዎችን በትክክለኛ ሰዓት እንደርሳለን : በሜዳ ላይ ይሁን በእርሻቸዉ ላይ።

ሶንግ ቫን: ከሲያትል የካምቦዲያ ስደተኛ – ለሲያትል የክሀሚር ማህበረሰብ በዋይት ሴንተር ማርች 12 በተዘጋጀው ክሊኒክ ላይ ሲሳተፍ (PHSKC/Ben Stocking)

ለማህበረሰብ ማረጋገጫ ማቅረብ

በርካታ የማህበረሰብ ድርጅቶች ክትባቶች ምንም እንኳ በሰፊዉ ተመርምረዉ ቢሆንም ደህንነታቸዉ የተጠበቀ አይደለም ብለዉ ለሚፈሩ ችግር እንደሌላዉ ለማረጋገጥ ሠርተዋል።  ስለ ክትባቱ ደህንነት ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ ኦንላይን ላይ በስፋት ይሰራጫል።

እንደዚያ ዓይነት ስጋት ያለቸዉ ሰዎች ዘንድ ለመድረስ እምነት ማግኘትን ይጠይቃል አሉ በርካታዎቹ ዉስን እንግልዝኛ የሚናገሩትን ስደተኞች እና ፈላሾችን የሚደግፈዉ የ Neighborhood House ሥራ አስፈጻሚ ዳሬክተር ጃኒስ ደጉቺ።

“ሠራተኞቻችን 14 ቋንቋዎችን ይናገራሉ” ብሏል ደጉቺ። “እንደሚታመን መልዕክተኛ ጭምጭምታዎችን በትክክለኛ መረጃ እንዋጋለን”

የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሲያትል  (ECS) ከ 600 ለሚበልጡ ሰዎች ክትባቶችን ያቀረበበት ሶስት የማህበረሰብ ክሊኒክ ኩነቶችን አስተናግዷል። “ስለ ዕድሉ እና የራሳቸዉ ቋንቋ በሚነገርበት ቦታ ላገኙት ድጋፍ እና ለጥያቄዎቻቸዉ መልስ ስላገኙ ሰዎች አመስግነዋል” ብለዉ ሃሳባቸዉን አጋርተዋል የ ECS መርሃ ግብር ማናጀር ጸጋ ደስታ።

“ስለ ክትባቶቹ ደህንነት በአማርኛ ባቀረብናቸዉ ስብስባዎች የዕድሜ ባለጸጋ ትዉልዶችን ለማሳመን እና ያላቸዉን ብዥታ ለማጥረት ችለናል። በዚህ ምክንያት በብዙ ቁጥር ነዉ ለመከተብ የመጡት” ደስታ እንደገለጹት።

ለተሳካ መድረስ የማህበረሰብ የቅርብ ቁርኝት ቁልፍ እንደሆነ ዶ/ር አኒሳ ኢብራሂም የኪንግ ካዉንቲ ሶማሌ ጤና ቦርድ (በእንግልዝኛ ብቻ ነዉ) ይስማማሉ።

“እምነት ለጠንካራ ግንኙነቶች የማዕዘን ድንጋይ ነዉ እና የሚገባዉ የሚያገኛዉ ነዉ” ዶ/ር ኢብራሂም እንዳሉት።

ከ 1 ሚሊዮን በላይ ገና ተጨማሪ አለ

አንድ ሚሊዮን የክትባት መጠን  ማቅረብ ጠቃሚ እምርታ ነዉ : ነገር ግን አንድ ሚሊዮን ሰዎች ከመከተብ ጋር ተመሳሳይ አይደለም። ያ ቁጥር ለአንድ ሰዉ የሚሰጥ ሁለተኛ ዙር ክትባትን ይጨምራል። ከ 2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ኪንግ ካዉንቲ ዉስጥ ይኖራሉ፤ ብዙ ተጨማሪ ገና ያልተሰራ ሥራ አለ።

እያንዳንዱ ሰዉ ክትባት እንዲያገኝ ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ከሆኑት መካካል 30 የሚሆኑ የኦዶም መካከለኛ ትምህርት ቤት ስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ቡድን አንዱ ነዉ።  እንደ Worth a Shot የሚባል ሃሳብ አንድ አካል የኮቪድ-19  ድጋፍ ምንጭ መጣጥፍ አዘጋጅተዉ ወደ 15 ቋንቋዎች አስተርጉመዋል።  

“በዚህ ዉስጥ ሁላችን አብረን ነን ሁላችን ደህንነታችን የተጠበቀ እስከምንሆን ማናችንም ደህና ልንሆን አንችልም” እንደ የኦዶም ቡድን አባል የሆነዉ መህር ግርዋል።  
“ይህን የ 1 ሚሊዮን እምርታ መድረሳችን በጣም አስደናቂ ነዉ” አሉ ግርዋል። “እያንዳንዱ ክትባት ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ አንድ ሌላ እርምጃ ነዉ። እያንዳንዱ ክትባት ወሳኝ ነዉ።”

አላን ላኢ ስለዚህ እምርታ እንዳንጸባረቀዉ: “ከአንድ ዓመት በፊት ኮቪድ ያለበት የመጀመሪያ ስቴት ነበርን እና ትኩረት ሁሉ እኛ ላይ ነበር። በቁርጠኝነታችንን እና ጥንካሬያችን በአገሪቱ ደህንነት ካላቸዉ ዉስጥ አንዱ ነን። አንድ ሚሊዮን በጉድጓዱ መጨረሻ ያለዉን ብርሃን ያሳየናል።”

የማህበረሰብ ጤና አንድ ላይ በመቀናጀት የኪንግ ካውንቲ ክትባት 1 ሚሊዮን እንዲደርስ ለረዱ ሁሉም ቡድኖች ምስጋናውን ያቀርባል::  ያለናንተ ይህን ማድረግ አንችልም ነበር።