አደገኛ እና መርዛማ አልጌ በኪንግ ካውንቲ ሃይቆች ውስጥ ተገኝቷል።

የማህበረሰብ ጤና – ሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ አልጌ ከሚታይባቸው የኪንግ ካውንቲ ሃይቆች አካባቢ ሰዎች እና የቤት እንስሳት እንዲርቁ ይመክራል። በፓርኮች እና ወንዝ ዳርቻዎች አካባቢ የተለጠፉ መመሪያዎችን ይከታተሉ።

ያስታውሱ – በሚጠራጠሩበት ወቅት፣ ከውሃ አካባቢ ይራቁ።

አልጌ የሚታይ ከሆነ፣ የቤት እንስሳት ውሃውን እንዲጠጡ ወይም አልጌው ጸጉራቸው ላይ እንዳይወጣ ይከላከሉ። ምንም እንኳን አልጌውን ባያዩትም፣ መርዞቹ ውሃ ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ። የቤት እንስሳዎ በኪንግ ካውንቱ ሃይቅ ውስጥ ከገባ ወይም በቅርበት ከሄደ የሚከተሉት ምልክቶች ስለመኖራቸው እንዲከታተሉ እንመክራለን፡ የጉልበት መቀነስ, አለመብላት, ማስመለስ, ተቅማጥ, የትንፋሽ መድከም, አካል ማንቀጥቀጥ። በመደበኛነት ምልክቶች ንክኪ ከተፈጸመበት በደቂቃዎች እስከ ሰአታት ውስጥ መታየት ይጀምራሉ። የቤት እንስሳዎ ከታመመ፣ የእንስሳት ሃኪምዎ ጋር ወዲያውኑ ይደውሉ።

በአዲስ አመት ቀን መዋኘት ወይም በ “ፖላር ድብ ፕለንጅ” (“Polar Bear Plunge”) ለመሳተፍ እያሰቡ ከሆነ፣ ስለአሁናዊው መረጃ ከዝግጅት አዘጋጆች ወይም የከተማ ፓርኮች ዲፓርትመንቶች መረጃ ይጠይቁ።